Endalegeta Kebede
.አንዳርጋቸው ጽጌ ተፈታ፤እሰይ! በኢትዮጵያ ምድር የበቀለ ሳር ቅጠሉ ሁሉ ሲናፍቀው የነበረ ዜና ነበርና የእሱ መፈታት ለፍትህ ለርትዕና ለሀገር ሲቆረቆሩ ለቆዩና መቆርቆር ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያንና አፍቃሬ ኢትዮጵያውያን መልካም የምስራች ነው፡፡ አንዳርጋቸው የማይሰፈር ዋጋ ከፍሏል፡፡አይተናል፤ሰምተናል፡፡ የመፈታቱ ዜና በህይወት ላላሉት ተቃዋሚዎቹ/አሳሪዎቹ ብቻ ሳይሆን ለሞቱትም አስደንጋጭ መርዶ ሊሆንባቸው እንደሚችል ሲገመት የቆየ ነው፡፡ እንግልቱ ደግሞ በውስን ዓመታት ብቻ የሚመደብ አይደለም፡፡ ከሃያ አምስት ዓመታት በላይ በኢህአዴግ ሲወገዝ፣ አሳዳጆቹ መቆሚያ መቀመጫ ሲያሣጡት የነበረ ሰው ነው፡፡ በደርግ ዘመንም አንዲሁ፡፡
አንዳርጋቸው ጽጌን ሳስበው ‹ነጻነት› የሚለው ቃል ብሄራዊ መዝሙር ሆኖ ወደ ጆሮዬ ይገባል፡፡ አንዳንዴ ‹ነጻነት› በሚል ርዕስ የሚታወቅ፣ሁላችንም ተቀባብለን ልንዘምረው የምንመኘው ተወዳጅና ዘመን አይሽሬ ነጠላ ዜማ ያለው ሁሉ ይመስለኛል፡፡ነጻነትን በቅጡ ሳያውቁ ነጻ እናወጣለን ስለሚሉ ታጋዮች ስለጻፈ ፣እሱም ለነጻነት በሚከፈል መስዋዕትነት ከመሪ ተዋንያን መካከል አንዱ ስለሆነ እንጂ በሌላ አይደለም፡፡አሁን ተፈታ! አሁንም ምስጋና ለእነ አቢይ አህመድ(ዶክተር)ይሁን!
አንዳርጋቸው የአዲስ አበባ ልጅ ነው - አዲስ አበቤ፡፡ ከአዲስ አበባ የወጣው በ1972 ነው - በወርሃ ጥር፡፡