ዩንቨርስቲቅ የግዕዝ ትምህርት ክፍሉን ከከፈተበት ከየካቲት 2010 ዓ.ም ጀምሮ ከ32 በላይ ተማሪዎች በቋንቋው ለመሰልጠን ተመዝግበዋል።
የባህርዳር ዩንቨርስቲው የውጭ ግንኙነት አና ትብብር
ዳይሬክተር አቶ ሞገስ አብረሀ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ለግአዝ ትምህረትና ለቋንቋው የምርምር
ማእከል የሚሆን ህንጻ ለመገንባት ዝግጅት እየተደረገ ነው።
የግዕዝ ቋንቋን አና በቋንቋው የተጻፉ ነገሮች ላይ ለሚመራመሩ ምሁራን ዩንቨርስቲው ድጋፍ አንደሚያደርግም ነው አቶ ሞገስ የገለጹት።
ትምህርቱ በፕሮፌሰር እና ፒኤች ዲ ደረጃ ቋንቋዉን በተማሩ መምህራን አና በመንፈሳዊ የግእዝ ትምህርት ረጅም ዘመን ባገለገሉ የሀይማኖት አባቶች እንደሚሰጥም አቶ ሞገስ ጠቁመዋል።
አሁን ላይ በመጀመሪያ አና ሁለተኛ ዲግሪ ስርአተ ትምህርት ተቀርጾ ስልጠናዉ የተጀመረ ቢሆንም፥ ወደ ፊት በ3ኛ ዲግሪ መርሀ ግብር ስልጠናውን ለመስጠት ታቅዷል።
የባህርዳር ዩንቨርስቲው ዩኒቨርስቲው የኦሮሞኛ ቋንቋ ለማስተማርም በዝግጅት ላይ መሆኑን ይታወቃል።
No comments:
Post a Comment