![]() |
| ግንቦት 20፣ 1983 ዓ.ም አዲስ አበባ (1) |
By Brook-Abegaz
ግንቦት 20 ቀን ሲመጣ ሁልጊዜም የሚታወሱኝ እነዚያ በልጅነት ዘመኔ ያየኋቸው ፀጉራቸውን አንጨብርረው አፋቸው
የሚያስተጋባ የኢህአዴግ ታጋዮች ናቸው። በዚያን ወቅት አያቴ “አየሁ ብያ” ትለኝና “አቤት” ስላት “ከደርግና
ከኢህአዴግ ማን ይሻላል?” ብላ ትጠይቀኛለች፤ እኔ ሁለቱንም ምን እንደሆነ ለይቼ ስለማላውቅ ከአፌ የመጣልኝን
እናገራለሁ፤ ታዲያ ይህን ጥያቄ በተለያየ ቀን ነው ደጋግማ የምትጠይቀኝ።

