01 Jun 2018
አንተነህ ቸሬ
በአጋጣሚም ይሁን ታስቦበት … ግንቦት በኢትዮጵያ ታሪክ
በርካታ ድርጊቶች የተፈጸሙበት ወር ነው፡፡ ኢትዮጵያ በግንቦት ወር ታዋቂ ልጆቿን ወልዳለች፤ ወደማይቀረው ዓለምም
ሸኝታለች፤ መሪዎቿን ወደ ሥልጣን አምጥታለች፤ ከሥልጣናቸው ሽራለች፤ አስከፊ ጦርነቶችን አስተናግ ዳለች፤ ከነዚህ
ታሪካዊ ክስተቶች በተጨማሪ ግንቦት ያልተለመዱ ክስተቶች የተስተናገዱበት ወርም ነው፡፡ ታዲያ ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋር
ልዩ ቁርኝት ያለውን ይህን ወር ከመሰናበታችን በፊት ኢትዮጵያ በግንቦት ወር ካስተናገደቻቸው ታሪካዊ ክስተቶች
መካከል ጥቂቶቹን ብቻ በአጭሩ ለመቃኘት እንሞክር፡፡