ኢትዮጵያ ከሰሐራ በታች ካሉ ዝቅተኛ የመጠጥ ውሃ ካላቸው አገራት አንዷ ስትሆን ለመጠጥ ውሃ ከምታመርተው ውስጥ 39 ከመቶው አገልግሎት ሳይሰጥ ይባክናል፡፡ በቀጣይም የመጠጥ ውሃ እጥረት ያጋጥማታል፡፡
ዶክተር ኢንጅነር አብዱላ ከማል በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር
ሲያብራሩ፤ በኢትዮጵያ ራሱን በዓመቱ የሚተካው የገፀ ምድር ውሃ 122 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ነው፡፡ ተከታታይ ጥናት
ባይደረግም የከርሰ ምድር ውሃው 36 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ እንደሆነ ይገመታል፡፡ ታዲያ በዓለም አቀፍ ስሌት አንድ
ሰው በዓመት የሚያገኘው የውሃ መጠን ከ1ሺ700 እስከ 1000 ሜትር ኪዩብ ከሆነ ወደፊት የውሃ እጥረት ይኖራል ፡፡